መግቢያ
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በከተማ አስተዳደሩበአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ሀላፊነት መሰረት በማድረግ የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት የሚያፋጥኑ ብቁ መሪዎችና ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚሰራ ቀዳሚ ተቋም ነው፡፡ አካዳሚው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በላቀ ደረጃ ለማሳደግ በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በከተማችን የእውቀት ሽግግርን ለማፋጠን፣ የሰው ኃይል አቅምን ለመገንባት እና በምርምር የተደገፉ መፍትሔዎችን ለማቅረብ የተቋቋመ የልህቀት ማዕከል ነው። አካዳሚያችን ዘመኑ የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎት በመቅሰም ረገድ ተመራጭ ተቋም የመሆን ራዕይ ሰንቆ እየሠራ ይገኛል።
የአካዳሚው ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች
ተልዕኮ /Mission/
በሰለጠነ የሰው ኃይል ለስልጠናና ምርምር አገልግሎት የሚውሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ለመንግስትና ለግል ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ክፍተትን መሰረት ያደረገ ስልጠና፣ ችግር ፈቺ ተግባራዊ ምርምር፣ የማማከር እና የማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ማጎልበት ነው፡፡
ራዕይ /Vision/
በ2022 ዓ.ም በከተማ አመራር አቅም ግንባታ ከአፍሪካ ካሉ አምስት ቀዳሚ የልዕቀት ማዕከላት አንዱ ሆኖ ማየት፡፡
እሴቶች /values/
ልዕቀት/Excellence/
ቅድሚያ ለጥራት/Quality First/
በቡድን የመስራት ባህል/Team Work/
የመፍትሄ አካል መሆን/Part of solution/
ስትራቴጂካዊ አጋርነት/Strategic Partnership/
ዋና ዋና የትኩረት መስኮቻችን
አካዳሚው የአዲስ አበባን የእድገትና የልማት ጉዞ ለማገዝ በሚከተሉት አራት ምሶሶዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡
ተግባራዊ ስልጠናዎች (Training):
ለከፍተኛ፣ ለመካከለኛና ለታችኛው እርከን አመራሮች እንዲሁም ለባለሙያዎች የአመለካከትና የክህሎት ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ የከተማዋን አስፈፃሚ አካላት ለውጤት ዝግጁ እናደርጋለን።
ችግር ፈቺ ምርምሮች (Research):
የከተማዋን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች መሰረት ያደረጉ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ፣ በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ግብዓቶችንና የመፍትሄ ሃሳቦችን እናቀርባለን።
የማማከር አገልግሎት (Consultancy):
ተቋማት አደረጃጀታቸውን እንዲያዘምኑ፣ የአሰራር ሰንሰለታቸውን እንዲያቀላጥፉና ውጤታማ ስትራቴጂዎችን እንዲነድፉ የላቀ ሙያዊ ድጋፍና የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን።
የማህበረሰብ አገልግሎት (Community Service):
አካዳሚው ካካበተው እውቀትና ልምድ በመነሳት፣ ከተማዋንና ነዋሪዎቿን በቀጥታ የሚጠቅሙ የተለያዩ የማህበረሰብ ተኮር አገልግሎቶችን በማቅረብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ይወጣል።
ለምን እኛን ይመርጣሉ?
ህጋዊ ስልጣን፡ በከተማ አስተዳደሩ በአዋጅ የተቋቋመና ሙሉ እውቅና ያለው ተቋም በመሆናችን።
ጥራትና ልህቀት፡ አገልግሎቶቻችንን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙና በዘርፉ በሰለጠኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች የምናቀርብ በመሆናችን።
ተግባር ተኮርነት፡ ስልጠናዎቻችንና ምርምሮቻችን የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታና ተቋማዊ ፍላጎት ያገናዘቡ በመሆናቸው።
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ – ለአመራር ልህቀትና ለተቋማዊ ስኬት!