“ተስፋ ን እንትከል” ፦ የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ::ሰኔ 26/2018 ዓ.ም፣

የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የ7ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በመቀላቀል 435 ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአካዳሚው የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አስፈራው በችግኝ ተከላው ለተሳተፉት የአካዳሚው አባላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል። አቶ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት፦ “ዛሬ የምንሰራው ስራ ሁሉ ለመጪው ትውልድ ተስፋ የሚሰጥ መሆን አለበት፤ እኛም ዛሬ ተክለን መተው ብቻ ሳይሆን፣ የተከልናቸው ችግኞች ለትውልድ ተስፋ እንዲሆኑ ከወረዳው አመራሮች ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን የክትትልና እንክብካቤ ስራ እንሰራለን” ብለዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፅዳትና ውበት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሕይወት ከበደ በበኩላቸው ዛፎች ለሰው ልጅ ህልውና ያላቸውን እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ መኖራቸውን አብራርተዋል። አክለውም የችግኝ ተከላው የተከናወነበት ቦታ መኖሪያ ቤቶችና ፋብሪካዎች የሚገኙበት አካባቢ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ቦታውን ለአካባቢ ጥበቃና ለተፈጥሮ ሚዛን መጠበቅ እጅግ ተመራጭ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።
አካዳሚው ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስኬትና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለችና የተዋበች ከተማን ለማስረከብ የበኩሉን ድርሻ መወጣቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።
አሻራችንን ለመጪው ትውልድ እናስተላልፋለን ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የንፍስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ አፍደል ሙኒር በበኩላቸው አካዳሚው የአመራሩና ባለሙያውን አቅም የሚገነባ ተቋም ነው። ከዚህ በፊት በስልጠና በጋራ ሰርተናል አሁን ደግሞ በዚህ መርሀ ግብር በመገናኘታችን ደስ ብሎኛል ብለዋል። አካዳሚው በቀጣይ ለወረዳው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ እለሁ ብለዋል።
Posted in Uncategorized.