****
9/03/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ አመራሮች ዳይሬክተሮችና ከፍተኛ አሰልጣኞች በተገኙበት የቻይና ቴንጂን ማኔጅመንት ኢንስቲቲውት ጋር በበየነ መረብ ስልጠና ስጥቷል።
አካዳሚው ከቻይና ቴንጂን ማኔጅመንት ኢንስቱት ጋር የጋራ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እየሰራ ይገኛል። በዚህም አካዳሚው ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች አንዱ የአመራር ስልጠና ላይ ትኩረት በማድረግ የአመራር ስልጠና ባህሪያት ፣ የአመራር አሰልጣኝ ሙያዊ ብቃትና ፈጠራን ያማከለ የአመራር ስልጠና በሚሉ ርዕሶች ላይ ስልጠና ተስጥቷል።
ስልጠናው አካዳሚው ለከተማዋ አመራር እየሰጠ ላለው ስልጠና አጋዥ እንደሆነ ተመላክቷል። በቀጣይም ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች በልዩ ልዩ የስልጠና ርዕሶች ላይ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።