***
08/03/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ለአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አመራሮች የአመራር ክህሎት በሚል ርዕስ ለሚሰጠው ስልጠና ለሰልጣኛች ኦረንቴሽን ሰጠ።
በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የከተማ አመራር ልማት ዘርፍ ም/ፕረዝዳንት ተስፍዬ ኤባ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር እንደ ሌሎች የሙያ ማህበራት አንዱ እንደመሆ መጠን ይህንን ተቋም በስልጠና በማገዝ እንዲጎለብት ማደረግ ግዴታችን ነው ብለዋል። አክለውም መምህራን የብዙ ልምድ ባለቤት እንደመሆናችሁና ከስራችሁ የወከላችሁት ብዙ እውቀት ፈላጊ ትውልድ ይዛችሁ የምትጓዙ በመሆኑ ስልጠናውን በጥሩ ስነ-ምግባር በመከታተል ወደ ትግባር በመቀየር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በሌላ በኩ ስልጠናው የተዘጋጀው መምህራን ክህሎታቸውን በማዳበር ያገኙትን እውቀት ትውልድ ላይ በማፍሰሰ ሚናችሁን መወጣት ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ም/ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አሊ ከማል ተናግረዋል። ም/ፕረዝዳንቱ አክለው መጪዋ ኢትዮጵያ ያለችው ትምህርት ቤት ውስጥ በመሆኑ ሀገር የሚረከብ ብቁ ትውልድ ለመቅረፅ የትምህርት ማህበረሰቡን ማብቃትና ማጠናከር ተገቢ ነው ብለዋል።
የመምህራን ማህበር ፕረዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላችው በሙያችን እውቀት ሊኖረን ይችላል አሁን የመጣነው ያለንበትን ቦታ እንዴት እየመራነው ነው ለሚለው የአመራር ክህሎት ስልጠና ያስፈልገናል ስልጠናውን በተለመደው የመምህራን ስነ-ምግባር መሰልጠን ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።