የሚያግባባን የጋራ ትርክት ላይ ትኩረት አድርገን መስራት እንዳለብን ተገለጸ።

****
ህዳር 05/2018 ዓ.ም፣
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ከአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ለተውጣጡ 140 ሴት አመራሮች በገዢ ትርክት ርዕስ ላይ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት በአካዳሚው የከተማ አመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ተስፋዬ ኤባ (ዶ/ር) አካዳሚው የከተማውን አመራሮችና ባለሙያዎች ለማብቃት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህ ስልጠና ሴቶች ከነጠላ ትርክት ወጥተው በጋራ ያለንን ትርክት ላይ ትኩረት በማድረግ እንዲሰሩ ክህሎታቸውን እንዲጨምሩ የሚያደርግ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም በጋራ ያለንን ሀብት፣ታሪክ እና እውቀታችንን ሰብስበን በመጠቀም ሀሳብ ለማመንጨት ስልጠናው ጠቃሚ መሆኑን ዶክተር ተስፋዬ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የሺ ወልዴ በበኩላቸው ስልጠናውን መውሰድ ብቻ ሳይሆን ሴቶች ከማህበረሰቡ መካከል በሁሉም ስራ ቀዳሚ ሆኖ መገኘትና ተለዋዋጭ በሆነው የከተማው ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ስራቸውን በተሳካ ሁኔታ እንዲሰሩ ስልጠናው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
Posted in Uncategorized.