ተጨማሪ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ የምርምርና ጥናት ቫልዴሽን ዎርክ ሾፕ ተካሄደ።

***
ሕዳር 04/ 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ተቋማት ደረጃ የአመራርና የስራ-አመራር የስልጠና ክፍተትና ፍላጎት ደሰሳ ጥናት አደርጓል።
አካዳሚው ለከተማ አስተዳደሩ ተሿሚ አመራሮችና የስራ አመራር አካላት (ዳይሬክተሮች፣ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች) ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጣቸውን ስልጠናዎች የመፈጸምና የማስፈጸም ክፍተትን መሰረት ያደረጉ የስልጠና ፍላጎቶችን ለመለየት ታስቦ የተሰራ ጥናት መሆኑን የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ መሪ ተመራማሪ አቶ ነጉስ መንግስቴ ገልጸዋል።
በዚህ ቫሊዴሽን የጥናቱ ዋና ዋና ግኝት ላይ እንደ ቀረበው የተሿሚ እና የስራ አመራር አካላትን ብቃት በምመለከት የእውቀት፣ የክህሎት፣ የባህሪና የስነ-ምግባር ክፍተቶች የሚታዩባቸው አካላት መኖራቸውን ያመላከተ ሲሆን እነዙህን ክፍተቶች ሊሞሉ የሚችሉ ዋና ዋና የስልጠና ርዕስ ጉዳዮች ለማመላከት መቻሉን አቶ ንጉስ አክለው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሁናዊ የሀይማኖት እንቅስቃሴ በሰላም ግንባታ ላይ ያለው ሚና የጥናት ፕሮፖዛል በመሪ ተመራማሪ በአቶ ሰለሞን ተፈራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
Posted in Uncategorized.