አካዳሚው የአመራሩንና የባለሙያውን ብቃት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ገለጸ።

****
ህዳር 04/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለተወጣጡ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በአመራር ክህሎትና በአፈፃፀም አመራር ርዕሶች ላይ ለ250 ለሚሆኑ ሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በስልጠና መክፈቻ ላይ የከተማ አመራር ልማት ዘርፍ ም/ፕረዝዳንት ተስፋዬ ኤባ (ዶ/ር) አካዳሚው በሁለት መልኩ ስልጠና እንደሚሰጥ ጠቅሰው የከተማ ተሸሚ አመራሮችንና ባለሙያዎችን የመፈፀምና የማስፈፀም ብቃት ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ 90% የሚሆኑ ሰዎች ለውጥ የሚያመጡት አንድ ተቋም ላይ በመቆየትና ልምድ በማካበት በሰው ሀብት ላይ በመስራት መሆኑን ዶ/ር ተስፋዬ ገልጸዋል።
አክለውም የተጠቀሱት የስልጠና ርዕሶችም በጥናት የተለዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ለአመራሮች እና ለባለሙያዎች እየተሰጠ መሆኑን ዶ/ር ተስፋዬ ገልጸዋል።

Posted in Uncategorized.