****
ህዳር 01/2018 ዓ.ም፣ የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለተወጣጡ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም ከአራዳ ክ/ከተማ ለተወጣጡ ሴት ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በስልጠና መክፈቻ ላይ የተገኙት
የከተማ አመራር ልማት ዘርፍ ሀላፊ ዶ/ር ተስፍዬ ኤባ አካዳሚው ሴቶችን በማብቃት በርካታ ስራ እየሰራ መሆኑንና ሰልጣኞችም የሚሰጠውን ስልጠና ወስደው ተግባር ላይ ማዋል አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሰልጣኞች መድረክ ላይ የተገኙት የስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምህረት ሀ/ መስቀል (ዶ/ር) ስልጠናው የአመራሩን የስራ አፈጻጸም እና የተግባቦት ክህሎትን ለማሻሻል በጥናት ተለይቶ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናውም ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለተወጣጡ አመራሮች በሲቪል ሰርቪስ የልጠና ክፍሎች እንዲሁም ከአራዳ ክ/ከተማን ለተወጡ ሴት ባለሙያዎች በአካዳሚው የስልጠና ክፍሎች እየተሰጠ ይገኛል።