የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን ጎበኙ።

****
ህዳር 08/2018 ዓ.ም
ጉብኝቱ አካዳሚ በከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የአመራሩንና የባለሙያውን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን በመገንባት ሂደት ለሚሰጠው አገልግሎት ልምድ ለመውሰድ የታለመ ነው።
አካዳሚው ወደፊት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን ተዘወሮ ጎብኝቷል።
አዲስ መሶብ በከተማ አስተዳደሩ የመጀመሪያውና የ13 ተቋማት አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል እየሰጠ ይገኛል። ማዕከሉ ለአገልግሎት ፈላጊው ማህበረስብ ምቹ ሁኔታን የፈጠረና ያለምንም እንግልት ባጭር ጊዜ አገልግሎት አግኝተው ረክተው የሚመለሱበት ማዕከል እንደሆነ መመልከት ተችሏል።
በማዕከሉ የሚሰጡ ሁሉም አገልግሎቶች ዲጂታላይዝና ወረቀት አልባ መሆኑ እንዲሁም የተቋሙ ሰራተኞች ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን መስፈርት ያሟሉና በተገቢው መንገድ ስልጠና ወስደው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ።
አዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ ለማድረግ ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድርግ ጉብኝቱ ጠቃሚ መሆኑ ተመላክቷል።
Posted in Uncategorized.