ጥቅምት 10/2015 ዓ.ም
የአካዳሚው ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ለሚ ተስፋ በውይይቱ ወቅት አካዳሚው የትምህርት፣ የስልጠና፣ የጥናትና ምርምር እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት በከተማ ውስጥ የሚገኙ አመራርና ባለሙያ እንዲሁም የተቋማትን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ገልጸው የከተማ አቅም ግንባታ አገልግሎትን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ እንደ KOICA ካሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊነው ብለዋል፡፡
የኮሪያን ኢንተርናሽናል ኮኦፕሬሽን ኤጀንሲ (KOICA) ምክትል ዳይሬክተር ሱን ያንግ ኪም በበኩላቸው ከአካዳሚው ጋር ተባበብሮ ለመስራት ኤጀንሲያቸው ዝግጁ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ በከፍተኛ አመራር ደረጃ የስምምነት ሰነድ በመፈራረምና ቴክኒካል ቡድን በማቋቋም ውጤታማ ስራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
ለኮሪያን ኢንተርናሽናል ኮኦፕሬሽን ኤጀንሲ ልኡካን ቡድን የአካዳሚው ተልዕኮና አሁን ያለበት ደረጃን በተመለከተ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን የስራ እንቅስቃሴውንም እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡
