ጥቅምት 7/2015 ዓ.ም
‹‹ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሀነታችን መገለጫ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ!›› በሚል መሪ ቃል 15ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የአካዳሚው አመራሮች፤ ሰራተኞችና ሰልጣኞች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡
በውይይቱ ላይ መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የአካዳሚው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደርቤ ፈለቀ በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ሰንደቅ ዓላማ ትልቅ ስፍራ ያለው ነው፡፡
ሰንደቅ ዓላማችን ከእናት እና ከአባቶቻችን በክብር ወርሰን በክብር ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፈው በልባችን ውስጥ ታትሞ የሚቆይ የብዝሃነታችን፣ የአንድነታችንና የሉዓላዊነታችን መገለጫ አርማና ምልክት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም ሰንደቅ ዓላማችን የመስዋዕትነት፣ የሉዓላዊነት፣ የአንድነት፣ የስነ-ልቦና፣ የአብሮነትና የብሔራዊ መግባባት መገለጫ አርማ ምልክታችን በመሆኑ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት የማክበርና የማስከበር ሃላፊነትና ግዴታችንን መወጣት አለብን ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ መጨረሻም የአካዳሚው አመራሮች፤ ሰራተኞችና ሰልጣኞች በተገኙበት ሰንደቅ አላማችንን በክብር ከፍ አድርጎ የመስቀል ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
