የተባባሪ አካላት ጥሪ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ለመንግስትና ለግል ተቋማት  ስልጠና በመስጠት፣ ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣ የማማከርና ማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት የአመራሩን፣ የባለሙያውን እና የተቋማትን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት አስፈጻሚ አካላትን መልሶ ማደረጀት አዋጅ ቁጥር 84/2016 የተቋቋመ የመንግስት ተቋም ነው፡፡ አካዳሚው የተሠጠውን ተልዕኮ እውን ለማድረግ ካሉት የውስጥ አሰልጣኞች፣ ተመራማሪዎች እና አማካሪዎች በተጨማሪ ከሌሎች ተቋማት ልምድና ብቃት ያላቸውን አሰልጣኞችን፣ ተመራማሪዎችና አማካሪዎችን አወዳድሮ የተባባሪ አሰልጣኞች፣ ተመራማሪዎችና አማካሪዎች ፑል ፈጥሮ በትብብር መስራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በመስራት፣ የማማከር አገልግሎቶችን በመስጠት እንዲሁም በስልጠና በማሰልጠን ልምዱና ብቃቱ ያላችሁ እና ከዚህ በታች የተገለጸውን መስፈርት የምታሟሉ ተባባሪ አካላት ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትብብር መስኮች እንድታመለክቱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ማሳሰቢያ

  • ከዚህ በፊት በአካዳሚው ተባባሪ የነበራችሁ በውጣው ማስታወቂያ መሰረት ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተጠየቁትን ማስረጃዎች አሟልቶ ያላቀረበ አመልካች ከውድድር ውጪ የሚደረግ ይሆናል፡፡

         ለበለጠ መረጃ፡ +251-11-667-22-98/ +251-11-667-34-73/ ይደውሉ

  • CV ብቻ መላክ ተቀባይነት አይኖረውም

የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ

Posted in Uncategorized.