ቀን 15/2/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ለመንግስትና ለግል ተቋማት ትምህርትና ስልጠና በመስጠት፣ ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣ የማማከርና ማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት የአመራሩን፣ የባለሙያውን እና የተቋማትን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት አስፈጻሚ አካላትን መልሶ ማደረጀት አዋጅ ቁጥር 84/2016 የተቋቋመ የመንግስት ተቋም ነው፡፡
አካዳሚው የተሠጠውን ተልዕኮ እውን ለማድረግ ካሉት የውስጥ አሰልጣኞች፣ ተመራማሪዎች እና አማካሪዎች በተጨማሪ ከሌሎች ተቋማት ልምድና ብቃት ያላቸውን አሰልጣኞችን፣ ተመራማሪና አማካሪዎችን አወዳድሮ የተባባሪ አሰልጣኞች፣ ተመራማሪዎችና አማካሪዎች ፑል ፈጥሮ በትብብር ለመስራት የተባባሪ አካላት ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም የአካዳሚውን የምልመላና መረጣ መስፈርት ያሟላችሁና የተመረጣችሁ መሆኑን እያሳወቅን ቅሬታ ያላችሁ አመልካቾች ከጥቅምት 15 ቀን 2017 ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ ለትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ም/ፕሬዝዳንት ቢሮ ቁጥረ 501 ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
የአካዳሚውን የምልመላና መረጣ መስፈርት አሟልተው የተመረጡ ስም ዝርዝር
አዲስ አበባ አመራር አካዳሚ